Saturday, November 22, 2008

ቅኔ ከድሮ

ቅኔ ከድሮ

ዋለልኝ መኮንን 1968

ቦረሳው ካሳ መካር አጡ
አንዳይሆን ሆነው ቀበጡ
ብዙ እያወቁ አንደጅል
የማይሆን ነገር መከጀል
ለድሃ እንዳይሆን እያወቁ
ዘውድ እምጡ ብለው ደረቁ
---------
ከለበሱ እይቀር ሱሪ
የጥንቱን ነበር የተፈሪ
ግና እይመችም ለስራ
አጣብቆ ይዞ በቀኝ በግራ


ደንዳር ደንሳሞ (1968)

ባውዳመቱ ዋዜማ
ስሰማ ከርሜ ላህየ ዜማ
በመጨረቫ ሲደክመኝ
ግዋደኞቼ መከሩኝ
ሊነጋ ነው እሉኝ
እሮገ ዘመን ልንቨኝ

ጸገየ ወይን ገብረመድህን (1968)

ነፎ መስዬ እባያ
ባዶ እጀን ቆሜ ከገበያ
እንገበገበኝ ንደቱ
ሲቨጥ ሲለወጥ ማየቱ
ብዙው በርካታው በጥቂቱ

No comments: